ብንተባበር ከወደቅንበት እንነሳለን
አላማዉ፡
ላለፉት እረጂም ዘመናት አንዳንድ ግለሰቦች ይህን አበይት ርዕስ ለመቃኘት ሞክረዋል፡፡ ነገርግን በተጨባጭ በማጠቃለያ ከነመፍትሄዉ በይፋ የተገለጠ ሃሳብ አልወጣም ወይንም ቢኖርም ጎልቶ እንዳይወጣ ሆኗል፡፡ ሁሉም በየግሉ ባለፉት ዘመናት የሆነዉን እና መሬት ላይ ያለዉን ለማስታረቅ ሲሞክር ሞጋች የሆኑ ሃሳቦች ይነሱበታል፡፡ እንደ አሰላሳዩ አይነት የሚነሱት ጥያቄዎች የተለያዩ ይሆናሉ፦ ያደገበት የማህበረሰብ አስተሳሰብ፣ የተማረበት ትምህርት ቤት፣ የሃገሩ የፖላቲካ መርሆ ሌሎችም ኩነቶች የበኩላቸዉን ተጽዕኖ ያበረክታሉ፡፡ ይህ አይነት የዐይምሮ መባከን ማየት የሚገባንን ማየት እንዳንችል ዐይምሮአችንን ሸብበዉ ይይዙታል፡፡
ይህን መሰረታዊ ጥያቄ መሬት የያዘ መልስ እንድናገኝለት ሁሉም ያገባኛል የሚል ግለሰብን ፣ ተቋምን በመጋበዝ ሁሉም የየበኩሉን በመሰንዘር የጠራ ምልከታ ላይ እንዲደረስ የዉይይት መድረክን በመዘርጋትና ጉባኤን በማዘጋጀት ሁኔታዎችን እናመቻቻለን፡፡
በዚህ ጉባኤ በየዘርፉ ለዚህ መሰረታዊ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሞከሩ ሃሳባችዉን በማጋራት፤ የጋራ መድረክ መፍጠር፡፡ ቀጣይነት እንዲኖሮው ጉባኤዉ ባመት ሁለት ግዜ ያካሂዳል፡፡
የጋራ መወያያዉ መድረክ አመቱን ሙሉ ክፍት ሲሆን፤ አጥኚዎች ስራቸዉን የጉባኤዎን ቀን ሳይጠብቁ በድህረ ገጽ ላይ በመስፈር ለዉይይት እንዲያቀቡ ማስቻል፡፡
እኛ ማነን
የሚጠቅሙና ባብዛኛዉ ሆን ተብለዉ በሚለቀቁ አሳሳች መረጃዎች የቀን ተቀን ኑሮችን የተሞላ ነዉ፡፡ የዚህ የተዋናበደ የመረጃ ሽክርክሪት ያሉብንን ችግሮች መፍትሄ ትክክለኛ አቅጣጫ እንዳንይዝ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በጋራ ሆኖ መፍትሄ መፈልግ አማራጭ በመሆኑ፡ አዘጋጁ ያሬድ ሲሳይ ነዋሪነቱ በኢትዮጵያ በንግድ ስራ የተሰማራ ይህን ጉባኤ እንዲጀመር ቀዳሚዉን ቦታ ይዟል፡፡
ለምን ወደቅን?
ጉባኤ
በቶሮንቶ ካናዳ
ግንቦት 2 2017 (May 10, 2025)
የጥቁር ሕዝቦች ሥልጣኔ ከነበረበት ከፍታ ወርዶ ዛሬ ካለበት ድቅድቅ ጨለማ ደርሷል፡፡ የዚህ ውድቀት ዉጤቱ ፤ ጥቁር ህዝብ ሰዉ መሆኑ ጥርጣሬ ዉስጥ እስኪገባና ጥቁር ሆኖ መፈጠር ሃጢያት እስኪመስል ድረስ በዘመኑ የሥልጣኔ መሪ ሃገሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሲንጸባረቅ ይታያል፡፡
የጥናትና የምርምር የትብብር ጥሪ
Call for paper
ምሁራኖች ፣ ጠበብት ፣ ተመራማሪዎች
በተጠቀሱት እርዕሶች ላይ ስራችሁን እንድታቀርቡ እንጋብዛለን፡፡
- ጥንታዊ የአፍሪካ የማህበረሰብ ስልጣኔዎችና ያስገኟቸዉ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች፣ በአስትሮኖሚ፣ በተምህርት ፣በምህንድስና፣በህክምና ወዘተ
- ለምን ወደቅን
ለተጫማሪ ንባብ