ኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ትብብር

የጥናት የምርምር ጥሪ

ምሁራኖች ፣ ጠበብት ፣ ተመራማሪዎች ፣
በተጠቀሱት እርዕሶች ላይ ስራችሁን እንድታቀርቡ እንጋብዛለን
Call for paper

ጉባኤ

ጉባኤ
በቶሮንቶ ካናዳ
ግንቦት 2 2017 (May 10, 2025)

የጥቁር ሕዝቦች ሥልጣኔ ከነበረበት ከፍታ ወርዶ ዛሬ ካለበት ድቅድቅ ጨለማ ደርሷል፡፡ የዚህ ውድቀት ዉጤቱ ፤ ጥቁር ህዝብ ሰዉ መሆኑ ጥርጣሬ ዉስጥ እስኪገባና ጥቁር ሆኖ መፈጠር ሃጢያት እስኪመስል ድረስ በዘመኑ የሥልጣኔ መሪ ሃገሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሲንጸባረቅ ይታያል፡፡ 

መዛግብት፣ ቅሪተዓካላት፣ ተዉፊቶች ወዘተ በቀደሙት ዘመናት የነበሩትን የማህበረሰብ ዕድገቶች፣ የአስተዳደር ጥበቦች፣ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ የዕደ ጥበብ ዉጤቶች ፣ የህክምና እና የመድሃኒት ትግበራዎች፣ የስነመለኮት(አስትሮኖሚ) ጥናቶች ወዘተ. አሁን ካለዉ በበለጠ ምጥቀት ላይ እንደነበሩ ያመለክታሉ፡፡ ታዲያ ይህ ሥልጣኔ የትገባ? 

ገዢዎችና ተባባሪዎቻቸው የራሳቸዉ ጥቅም ለማበልጸግ ወይም የማህበረሰብ እድገት ያፋጥናል ብለዉ ያሰቡትን መርህ ሲተገብሩ ዘመናት ተፈራርቀዋል፡፡ በዓለማችን ከተመሰረቱበት (ማለትም እንደሃገር ከቆሙበት) ግዜ እስካሁን በዘለቄታነት የቀጠሉ ማበረሰቦች አንድ ወይም ሁለት ቢሆኑነዉ፡፡ እነዚህ ሃገራት ታሪካቸዉ የሚያሳየዉ ባንድ ወቅት በሁሉም መስክ ቀዳሚ ስፍራ የነበራቸዉና ሌሎች ሃገሮችን በማሰልጠን ከፍተኛ ሚናን ሲጫወቱ እንደነበረ ነዉ፡፡

የቀን ተቀን ኑሮን የማሸነፍ ትግል፣ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚለቀቁ የሰዉን ልጅ አዕምሮን የሚያደነዝዙ ሃሳቦችና ድርጊቶች፤ ቆም ብለን ለምን እንደወደቅን ለማሰብ ፋታ አልሰጡንም፡፡ እራሳችን የፈጠርናቸዉ ችግሮች፣ የዉስጣዊና ዉጫዊ ተጽዕኖች መደራረብ፤ አጠገባቺን ያለዉን ብዙ ዉስብስብ ያልሆነዉን የተፈጥሮ ክስተት እንኳን ለመገንዘብ አልስቻልንም፡፡ ይህን ስንል ግን ባለፉት ዘመናት አልጠየቅንም ማለት አይደለም፡፡ ጠይቀናል፡፡ ብልጽግናን የሚያመለክቱ ጽንሰሃሳቦችና በተቃራኒዉ የጥቂቶችን መበልጸግና የብዙሃኑን መዉደቅ የሚያበረታቱ ጽንስሃሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡ መልካሙ መንገድ አይሎ እንዳይወጣ የተለያዩ ሃይላት ሁኔታዉ በፈቀደላችዉ መጠን ሲያድበሰብሱት ቆይተዋል፡፡ እንደየዘመኑም ከመልካሙ ሃሳብ ጋር ተመሳሳይ የሚመስል ግን አሳሳች የሆኑ ጽንሰሃሳቦች እንዲሰራጩ በማድረግ የወደቅንበትን መክኒያት እንዳናዉቅ ብዙ ደባ ተደርጓል እየተተደረግም ነዉ፡፡

የወደቅንባቸዉን ምክኒያቶች ጥርት ባለ መልኩ ማሳየት እንድንችልና ለመፍትሄዉ ሃሳብ መዘጋጀት እንድንችል፡፡ ሁሉም የጥቁር ህዝብ በዚህ መድረክ ላይ በመሳተፍ፤ በጋራ እንድንወያይ እጋብዛለሁ፡፡

ጉባዔዉን በአካል በመገኘት ወይንም በቪርችዋል መሳተፍ ይቺላሉ፡፡

ቅድሚያ ምዝገባ ዋጋዉ መደበኛ ምዝገባ ዋጋዉ
በአካል እስከ ጥር 30 2017
Till Jan 30, 2025
CAD 30 ከየካቲት 1 2017 ጀምሮ
(Feb 8,2025)
CAD 50
ቪርችዋል እስከ ጥር 30 2017
Till Jan 30, 2025
CAD 20 ከየካቲት 1 2017 ጀምሮ
(Feb 8,2025)
CAD 50

ተጋባዥ እንግዶች

ተጋባዥ እንግዶች
ተጋባዥ እንግዶች